❝ ኪዳነ ምሕረት ❞
እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ኪዳነ ምሕረት ወርኃዊ በዓል አደረሰን!!ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በነበረበት በዚያች አስጨናቂ ሰዓት፣ለሚወደው ደቀ መዝሙር ለቅዱስ ዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” (ዮሐ. ፲፱፥፳፯) በማለት የሰጠን ስጦታ የአደራ ቃል ብቻ ሳይኾን በቅዱስ ዮሐንስ ውክልና አማካይነት ምእመናን ኹላችን ያለ እናት እንዳንቀር የተበረከተልን ታላቅ የእናትነት ስጦታ ነው።
ይኽችን የጌታ ስጦታ የኾነችን እናታችን ንጽሕት ድንግል ማርያምን፣እንደ ኢትዮጵያዊው ታላቅ ሊቅ መምህር እና ቅዱስ ጻድቅ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ “ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ፤ ድንግል ኾይ ከተወዳጅ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ እኔ ነይ ትባርኪን ዘንድ” በማለት ወደ ሕይወታችን በማስገባት የጽድቃችን መሸጋገሪያ ድልድያችን እናድርጋት።
የእናታችን የንጽሕተ ንጹሐን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ወላዲተ አምላክ ምልጃና ጸሎት አይለየን
