30 አዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነት አገኙ
ግንቦት 09 2018 ዓ.ም
የስ/ሐ/ተ/መ/ሚዲያ (አ/አ)
በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ጀሞ ደብረ ብርሃን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
30 አዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነት አግኝተዋል።
በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለአዳዲስ አማንያን የሚከናወነው የቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓትም ተፈፅሞላቸዋል።
በመርሐ ግብሩ መልአከ ሰላም አለማየሁ ተፈራ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ፤ ቆሞስ አባ አፈወርቅ ዮሐንስ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የለሚኩራ ክፍላተ ከተማና በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሦስቱ ክፍላተ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ፣ መልአከ ብርሃን ቀሲስ መልካሙ ጌትነት የጀሞ ደብረ ብርሃን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ ካህናት ፣ መምህራን እና ምእመናን ተገኝተዋል።
በዚሁ በጀሞ ደብረ ብርሃን አቡነ ተክለ
ሃይማኖት ቤተክርስቲያን መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎትና ቡራኬ 75 አዳዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነት ማግኘታቸው ይታወሳል።
© EOTC_TV
